በፍቃዱ ኃይሉ ከአርባ ቀናት እስር በኋላ ዛሬ ተለቋል

በፍቃዱ ኃይሉ ከአርባ ቀናት እስር በኋላ ዛሬ ተለቋል፡፡ #Ethiopia
ለ VOA Amharic ፕሮግራም በሰጠኸው ቃለመጠይቅ ምክንያት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ተችተሃል በሚል ከመኖሪያ ቤቱ አካባቢ ታስሮ የነበረውና በአዋሽ በሚገኘው የወታደር ማስልጠኛ ካምፕ የነበረው በፍቃዱ ኃይሉ ከአርባ ቀናት እስር በኋላ ዛሬ ተለቋል፡፡
በተጨማሪም መምህር እና የበይነ መረብ አምደኛው ስዩም ተሾመ ፣ ደራሲና ጋዜጠኛ ሰለሞን ስዩም፣ እያስፔድ ተስፋዬ ፣ ብሌን መስፍን እና ሌሎችም የኅሊና እስረኞች ቤተሰቦቻቸውን ተቀላቅለዋል፡፡