ከዚህ በላይ ውርደት የለም! (ነፃነት ዘለቀ)

ዕለቱ ኅዳር 5 ቀን 2009ዓ.ም ነው፡፡ ቦታው ኮተቤ በሚባለው ሰሜን አዲስ አበባ አካባቢ ሲሆን በመንግሥት የተፈጸመው ድርጊት ደግሞ እጅግ የሚዘገንንና በዓይነቱም የመጀመሪያ ሊባል የሚችል  ነው፡፡ እንዲህ ያለው አስነዋሪ ተግባር በዮዲት ጉዲትና በግራኝ አህመድ መፈጸሙ ቢነገር አይደንቅም፡፡ ምክንያቱም እነዚያ ሰዎች አነሳሳቸው በለዬለት ሁኔታ ኦርቶዶክስን ለማጥፋት ነበርና፡፡ ለነገሩ ሕወሓትም “ኦርቶዶክስንና አማራን አርቀን መቅበር የትግላችን ማዕከላዊ አጀንዳ ነው፤ ይህንንም በተግባር አሳይተናል” እያለ ከጥንት እስከ አሁን ስለሚፎክር ከነዚያ ጉዶች የሚለይበት ነገር የለም፡፡ ይሄን ጠባያቸውን እንዴት ዘነጋሁት በል? በጠቀስኩት አካባቢ በቅዱስ ጊዮርጊስ ስም የሚጠራ አንድ ቤተ ክርስቲያን አለ፡፡ የዚህ ቤተ ክርስቲያን ደብር ከአካባቢው ሕዝብ ጋር በመመካከር በደብሩ አጠገብ ሌላ ቤተ ክርስቲያን በመቃኞነት ይሠራና የቅድስት አርሤማንና መቅደላዊት ማርያምን ጽላቶች መስከረም 29 ቀን 2009ዓ.ም በሥርዓተ ንግሥ በከፍተኛ ይባቤ ያስገባል፡፡ በነገራችን ላይ ትንሽ ዘግየት ብልም ይህን መረጃ በቦታው ከነበረ ሰው ነው ያጠናቀርኩት –  እናም እንደተነገረኝ ከሆነ አዲሱ ቤተ ክርስቲያን የተሠራበት ቦታ ከአካባቢው ነዋሪ ገበሬዎች በነፃ የተሠጠ ሲሆን ከወረዳው ጽ/ቤትም ህጋዊ የግንባታ ፈቃድ ለሕንፃ ቤተ ክርስቲያን አሠሪ ኮሚቴ ተሰጥቷል፡፡ በመሃል ግን ተቃዋሚ ይነሣል፡፡ የተነሣው ተቃዋሚ ወረዳውን አልፎ ወደ ክፍለ ከተማ በመሄድ የማስፈረሻ ማስጠንቀቂያ ወረቀት እንዲላክ ያስደርጋል፡፡ የቤተ ክርስቲያኑ አስተዳደር ግን የአፍርሱ ደብዳቤ ቢደርሰውም ሳያፈርስ ይቆያል፡፡ ሃይማኖታዊ አገልግሎቱንም ይቀጥላል፡፡ ሰኞ ዕለት፣ ኅዳር 5/2009 ከጧቱ ሁለት ሰዓት አካባቢ በዚህ አዲስ ቤተ ክርስያን ቅዳሤ ተገብቶ አሃዱ አብ አልፎ እግዚኦታውም ተገባዶ ዕርገት ሊወርድ ሲል ማለትም ሥጋ ወደሙ ሊፈተት ሲቃረብ የክፍለ ከተማው አፍራሽ ግብረ ኃይል በሦስት ትላልቅ መኪኖች ተጭኖ በፌዴራል ወታደርና በፌዴራል ፖሊስ ታጅቦ ቅጽረ ግቢው ይደርሳል፡፡ ይህ የአይሁድ መንጋ ግቢው ውስጥ እንደገባ ልክ ሰሜን ጎንደር የነፃነት አርበኞች የጦር ቀጣና ውስጥ የገባ ያህል በመቁጠር ቀዳሽም አስቀዳሽም ባለበት ቀጥ ብሎ እንዲቆም በማዘዝ ዮዲት ጉዲታዊው የጥፋት ሠራዊት ጽላቶቹ ወዳረፉበት ወደ ቤተ መቅደሱ ጠበንጃውን ወድሮ ይገባል፡፡ መጮህም መናገርም መንቀሳቀስም እንደማይፈቀድ ለሁሉም ከባድ ማስጠንቀቂያ ይሰጣል – ማስጠንቀቂያውን የሚተላለፍ ቢኖር እንደሚገደልም ይነገራል (ኢትዮጵያ እኮ ከሦርያ የምትለይበት ነገር ነው የጠፋኝ አሁንስ፤ ዓለም ሳያውቅልን እንደዚህ የለየለት ሲዖል ውስጥ እንኑር??)፡፡ አፍራሾቹ የቤተ ክርስቲያኑን ግድግዳም ጣሪያም ሲገነጣጥሉ ታጣቂዎች ቀሳውስቱና ምዕመናኑ ላይ መሣሪያ ወድረው አንዳች እንቅስቃሴ እንዳያደርጉ ይጠብቃሉ፡፡ በዚህ መሀል ግን ካህናቱ ከፈለጉ ታቦቶቹንና ንዋየ ቅድሣቱን ሊያወጡ እንደሚችሉ በጥፋት ሠራዊቱ የአጋንንንት አለቃ ይነገራቸዋል (አቤት በዚያች ቅፅበት በዲያብሎስ መንደር የሚደረግ ደስታና ፈንጠዝያ!)፡፡ (በዚህ መሀል ግን የጊዮርጊስ ጠበል አጥማቂና በወቅቱ በንፍቅነት ይቀድሱ የነበሩ አንድ መነኩሤ ካህን በእግር አውጪኝ መሸሻቸው ለትዝብት እንደዳረጋቸው ማስታወስ እፈልጋለሁ፡፡ የክርስቶስን መስቀል የታጠቀ፣ በቁሙ ሞቱን ያወጀ ሰው አርአያ መሆን ሲገባው እንዲያ ማድረጉ ሃይማኖቱ ከሥር ብቻ ሣይሆን ከጫፍም ብል እንደበላው ይጠቁማል – ‹መንኮሰ› ማለት ‹ሞተ› ማለት ነውና)፡፡ እግዚአብሔር በቶሎ ካልታደገን ይህች ኢትዮጵያ ልትጠፋ – እስካሁን ካልጠፋች ማለት ነው – ገደል አፋፍ ላይ ደርሳለች፡፡ እንዲያው ከዚያም አልፋ የገደሉን ወገብ ሳታጋምስ የቀረች አይመስለኝም፡፡ ለማንኛውም በቤተ ልሔሙ በኩል በሥውር ያልሸሹ ካህናት ተረባርበው ጽላቶቹንና ልብሰ ተክህኖዎችን አወጡ – ልክ እሳት የተነሣ ያህል፤ ወያኔ ከእሳት በለጠ ማለት እኮ ነው፡፡ ሁለት ዲያቆናት ግን በማጉረምረማቸው የጎንደርና የጎጃም እንዲሁም የወለጋና የአርሲ ወጣቶች እየቀመሱት ያሉትን ዱላና ቆመጥ ተቋደሱ፤ ተሰባበሩናም ለወጌሻ ቀለብ ተዳረጉ፡፡ ግን ለክፉ የሚሰጥ ማለትም እስትንፋስን የሚገታ አደጋ አልደረሰባቸውምና አሁን እያገገሙ ናቸው፡፡ የደብሩ አለቃ ግን እስካሁን በእስር ላይ እንደሚገኙ ታውቋል፡፡ ሊያውም ክፍለ ከተማው እንዲፈቱ አዞላቸው ፖሊስ እፈልጋቸዋለሁ ብሎ ነው ያልፈታቸው ይባላል፤ ምናልባት “ቤተ ክርስቲያን በማነጽ የአሸባሪነት ተግባር ስላገኘኋቸው በኮማንድ ፖስቱ የተሃድሶ ማዕከል ለስድስት ወራት ታስረው ካልታደሱልኝ አልለቃቸውም” ብሎ ሊሆን ይችላል፡፡ መጠርጠር ነው፡፡ በዚህ የወያኔ ዘመን አሸባሪ ያልሆነ ዜጋ እኮ የለም – ውሻና ድመቱም በሽብር ሳይጠረጠሩ ይቀራሉ ብላችሁ ነው?፡ ቡና ቤት እየተዝናናህ ያዘዝከው ድራፍት ቢዘገይና “እንዴ! አሁንስ አላበዛችሁትም? ለምንድን ነው ድራፍቱን የምታዘገዩት” ብለህ በቁጣ ስሜት ብትናገር እንኳን “በጩኸት የአካባቢን ሰላም በመንሳት የሽብር ተግባር” ልትከሰስ ትችላለህ፡፡ የዛሬን አያድርገውና ‹ወይ መአልቲ!› አለ ትግሬ? የት ሄደን እንኑር? ምን ይዋጠን ኧረ! ልብ በሉ፡፡ ሃይማኖትን እስከዚህ የደፈረ የኢትዮጵያ ገዢ እስካሁን የለም፡፡ ደርግ ነው በዚህ ይታማ የነበረው፡፡ እሱም ቢሆን በቅዳሤ ሰዓት ቤተ ክርስቲያንን ወርሮ ቤተ መቅደስን አላፈረሰም – ደርግ በክፉ ሥራው ምክንያት ቢጠፋም ባልሠራው ሊታማ አይገባም፡፡ ባይሆን አባሎቹ ከሃይማኖት እንዲወጡ፣ ልጆቻቸውን ክርስትና እንዳያስነሱ … በእጅ አዙር ተፅዕኖ ያደርግ ነበር፡፡ ከዚያም ባለፈ ሕዝባዊ ስብሰባዎችንና ጉባኤዎችን ሃይማኖታዊ ድርጊያዎች በሚከናወኑባቸው ሰዓት ሆን ብሎ እያደረገ ለምሣሌ በከተራ ዕለት ታቦታትን አጅበው ወደ ማደሪያቸው የሚሸኙ ምዕመናን እንዳይኖሩ በዘዴ ሃይማኖቱን ይተናኮል ነበር፡፡ ረቡዕና ዐርብ ድግስ በመደገስ ጧሚና በላተኛን ይለይና ጧሚን በኋላ ቀርነት፣ በላተኛን በተራማጅነት ይፈርጅ ነበር፡፡ ግን ግን ያ ሁሉ ሸርና ፀረ-ሃይማኖተኝነት ቀብሩን አፋጠነው እንጂ አልጠቀመውም፡፡ ክፉም ለራስ ደግም ለራስ፡፡ የሠራኸውን ተቀምጦ ታገኘዋለህ፤ ማንም አይወስድብህም፡፡ ይህኛው ወያኔ ትግሬ የሚባለው ግን እጅግ ይለያል፡፡ ዋናውን የፕትርክና ቦታ በአንድ ትግሬ ዐረማዊ ሰው አስያዘ፡፡ ይህ ዐረማዊ የዲያብሎስ አሽከር የፊተኛውን ወምበዴ ትግሬ ጳጳስ – ሆ! የበሰበሰ ዝናብ አይፈራም ማለት እንዲህ እንደኔ ነው – በልጆቹ በወያኔዎች ጉልበት በመተካት ቤተ ክርስቲያንን እያፈረሰ ይገኛል፡፡  ዕድሜ የማያስተምራቸው ዘረኞቹ የትግሬ ጳጳሳት ከክርስቶስ መንግሥት ይልቅ የወያኔው ምድራዊ ጠፊ መንግሥት በልጦባቸው ይሄውና ሕዝበ ክርስያቲንን በተኩላና በቀበሮ በጠራራ ፀሐይ እያስፈጁት ይገኛሉ፡፡ ቤተ ክርስቲያን በአሁኑ ወቅት የተወረረችው – ሆን ተብሎና በጀትም ተበጅቶለት – በጌይ ዘማሪያንና ሰባኪያን ነው፡፡ በኔ ለመፍረድ ከመቸኮል መዛግብትን ገላልጣችሁ አንብቡ፡፡ ወያኔ ከተሳካለት አንዱና ዋናው ቤተ ክርስቲያንን ማጥፋት  ነው-  ድራሹዋ ጠፍቷል፡፡ የሚያምር ሕንጻ ቤተ ክርስቲያን ስለተገተረ፣ ከበሮ ስለተመታ፣ ጸናጽልና ሻውራ ስለትንሹዋሹዋ ቤተ ክርስቲያን አለች የምትል ከሆነ ተሳስተሃል – የእግዚአብሔር ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ደግሞ ያንተና የኔ (ንጹሕ) ልቦች እንጂ ግዑዙ አሸዋና ስሚንቶ ከድንጋይ ጋር ኅብረት ፈጥረው ስለቆሙ አይምሰልህ፡፡ ቤተ ክርስቲያን አሁን አለች የሚያስብላት ነገር ምን ቀራት? ምድረ ማይም ካድሬ ትግሬ ወያኔ ረጃጅም ካባና ዕርፍ ዕርፍ የሚህል መስቀል እየያዘ ቤተ ክርስቲያንን ከጫፍ እጫፍ ወርሮ በሽርሙጥናና በሴሰኝነት፣ በሙስናና በዘረፋ፣ በዘረኝነትና በኑፋቄነት፣ በዋልጌነትና በሰካራምነት፣ በምዕራባዊነትና በኢሞራላዊነት… ምን አለፋችሁ ሰይጣን ባሉት ሥጋዊ ወመንፈሣዊ የጦር መሣሪያዎች ሁሉ ሰቅዞ ይዟታል፡፡ ወያኔ ቀላል የዲያብሎስ ቀኝ እጅ እንዳይመስላችሁ፡፡ ወያኔን ሰዎች ሲንቁት በተለይ አሁን አሁን ይገርመኛል፡፡ የናቁት ወንድ ያስረግዛል አሉ – ሊያውም መንታ መንታ! የወያኔማ እንደቻይኖቹና ከነሱም በበለጠ መጥፎ አስረጋዥ ነው፡፡ ለነገሩ የርሱም አወዳደቅ ከሮምም መቶ እጅ የበለጠ ነው – በርግጠኝነት!! ምድረ ሀበሻ እንግዲህ ጉድሽን ዕወቂ፡፡ የወያኔና በአምሣሉ የፈጠራቸው የቤተ ክህነት አለቆች ሕዝብን የመናቅ ዐመል ቀላል ነው – ተላምደነዋልም፡፡ ግን ግን በዚህ መልክ ቅዳሤ የተገባበትን ቤተ ክርስቲያን መድፈር ምን ስም ልንሰጠው እንደምንችል ግራ ያጋባል፡፡ ፈጣሪ ሆን ብሎ ትቶት ይሆናል እንጂ፣ ምናልባትም እምነታችን ተሸርሽሮ እኛም ከፈጣሪ መንገድና ትዕዛዝ ስለወጣን ይሆናል እንጂ በዚህ ድርጊታቸው መብረቅ በታዘዘና ወዲያውኑ ፀጥ ባደረጋቸው ነበር፡፡ ግን ሁላችንም የተሳሳትን በመሆናችን ይመስላል አንዳችንን ከአንዳችን ለይቶ ጣልቃ መግባት የፈለገ አይመስልም፡፡ በበኩሌ ጉድ አልኩ፡፡ እናንተስ? 

ምንጭ ECADF